Sunday, September 16, 2012

ውሸት ሲደጋግሙ እውነት የመሰላቸው ወያኔዎች


ጌዲዮን ደሳለኝ ከኖርዎይ
ይገርማል እኔ በበኩሌ ይኀው ነፍስ ካወኩ ጀምሮ ከወያኔ እውነት የሰማሁበት ቀን አንድም ግዜ ትዝ አይለኝም፥ ውሸታቸው ለራሳቸውም እውነት እስኪመስላቸው ድረስ ነው፥፥Forcing people to mourn Meles Zenawi's death in Ethiopia
ታድያ ሌላውም የኢትዮጵያ ህዝብ እንደነሱ ውሸትን እውነት አድርጎ እንዲቀበል ይፈልጋሉ፥ እስከማስገደድ ድረስ፥፥
ሰዎችን የተለያየ የውሸት ማስረጃ እያቀረቡ ማሰር ከመዘውተሩ ብዛት እውነት እየሆነ ማቷል፥
ሲሳይ አጌና ለእትም ያቀረበው ያቃሊቲው መንግስት የሚለው መፅሃፉ ለዚህ በጣም ብዙ ማስረጃ ይሰጠናል፥
በመጀመርያ ለሲሳይ ትልቅ ምስጋና ይቅረብልኝ፥፥
የወያኔ መንግስት ምን ያህል ለተንኮል ቆርጦ እንደተነሳ፥ስልጣኑን ላለማጣት የት ድረስ እንደሚቆፍር ለመረዳት አያዳግትም፥ የሚያቀነባብሩአቸው ውሸቶች ደሞ ከትልቅ ውሸት እስከ ተራ ውሸት ሊሆን ይችላል፥ ይሄ ለወያኔዎች Normal ነው፥፥
የሚገርመው ግን ህዝቡ ሊጠረጥር ይችላል ብለው እንኩአን አለማፈራቸው ነው፥፥
እስቲ ወደሲሳይ አጌና መፅሃፍ መለስ ላርጋችውና  ገፅ 372 ተመልከቱ፥
ከ 1997 ምርጫ በሁዋላ በተከሰተው ብጥብጥ ምክንያት ስለተከሰ ፥ሰለተጎዱት፥ስለተገደሉት፥ስለታሰሩት ሰዎች የሚያጣራ 10 አባላት ያሉት ኮሚሽን ተቁዋቁሞ ነበር፥ የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የነበሩት ዳኛ ፍሬህይዎት ሳሙኤል ነገሩ ውስብስብ ሲልባቸውእንዲህ አይነት ማጭበርበር መንግስትን አይመጥንም ብለው እርፍ፥፥
ገፅ 363 ስንመለከት ደሞ 
ይህን ሪፖርት መቀየር ህሊናዬ ስላልተቀበለው ከሃገሬ ተሰደድኩ ያሉት ደሞ ምክትል ሰብሳቢ የነበሩት ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ሲሆኑ ዋና ሰብሳቢው አቶ ፍሬህይዎት ከሃገር ከወጡ በሁአላ በውና ሰብሳቢነት ካገለገሉ በሁዋላ እሳቸውም በደረሰባቸው ጫና ሪፖርቱን ይዘው ከሃገር ለመሰደድ በቅተዋል፥፥
እረ ስንቱን መዘርዘር ይቻላል፥
መፅሃፉ ላይ ብዙ መረጃዎች ቀርበዋል በጣምም ጠቃሚዎች ናቸው በዚህ አጋጣሚ መነበብ ያለበት መፅሃፍ ነው፥
ለነገሩ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ ከሰሩዋቸው ሴራዎች ትንሽዋን ላንሳ ብዬ ነው እንጂ ተነግሮ አያልቅም፥
ብቻ ምን አለፋችው የወያኔ ውሸት ይሄ ነው ተብሎ አያልቅም ከላይ እንዳልኩት ከትልቅ ውሸት እስከ ተራ ውሸት፥
ሰሞኑን ደሞ የአምባገነኑ መለስ መሞት ውሾቻቸውን ድምብርብራቸውን ነው ያጠፋው፥ ብዙ አስገራሚ የሃዘን አይነት አስተውለናል፥ ምናልባትም በአለም ትልቁ የተቀነባበረ የለቅሶ ስርአት ልለው እችላለው፥ አላማው ባይገባኝም ያሳፍራል፥ የገረመኝ ደሞ ካሳንችስ አካባቢ የተወሰኑ ጭፈራ ቤቶች ሙዚቃ ከፈታችው ተብለው ታሸጉ ሲባል መስማቴ፥
ብቻ ይገርማል የተለያዩ ሰዎች አስተያየትም ግርም ይላል፥ የጎዳና ተዳዳሪ ነኝ የሚለው እያለቀሰ መለስ እኮ ለኛ ብዙ እቅድ ነበረው፥ከአሁን በሁአላ safe አደለንም ሲል ተደምጧል፥ አንድ ግለሰብ ደሞ ምነው እሱ ኖሮ ዕኔ በሞትኩ ሲል በetv.  ታይቷል፥ባዶ ሬሳ ሳጥን ፊት ለፊት ተንበርክኮም ሲሰግድ የታዩም አልጠፉም፥  የአዜብማ በቃ ይሄን ጉድ የአለም መንግስት ይመልከትልኝ የምትል ነው የምትመስለው፥፥
እኔ ኢትዮጵያዊ ሰው ለሚያመልከው አምላክ ሲሰግድ ነው የማቀው፥፥ ለጥቅም እንኳን ቢሆን አምላክን ትቶ ለሰው ለዛውም የኢትዮጵያን ህዝብ ለ 21 አመት ለገደለ፥ ላሰረ፥ላሰደደ፣ ያገርን ጥቅም ለሸጠ ከሃዲ መስገድ በምድርም በሰማይም ገሃነም ያስገባል፥፥
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

Ethiopian Ruling Party Confirms Hailemariam as Meles’s Successor By William Davison, Bloomberg News | September 16, 2012

Ethiopia’s ruling party confirmed acting Prime Minister Hailemariam Desalegn as the successor to the late Prime Minister Meles Zenawi.
Meles, who led Ethiopia for 21 years and who oversaw one of Africa’s fastest-growing economies, died on Aug. 20 from an infection contracted while he was recovering from an undisclosed illness. Hailemariam, Meles’s deputy in the Ethiopian Peoples' Revolutionary Democratic Front and a former foreign minister, took over in an acting capacity the next day.


“Out of three candidates, Hailemariam has got the unanimous vote of council members and will serve as chairman of EPRDF and Demeke Mekonen will serve as well as deputy chairperson of EPRDF,” Communications Minister Bereket Simon said in the capital, Addis Ababa. “Whoever’s elected as chair and deputy chair of party will automatically be the nominees for the premiership and deputy premiership. So both Mr. Hailemariam and Mr. Demeke will represent the party and be candidates and be presented to parliament for approval when it starts its formal session in early October.”
Ethiopia, the continent’s second-most populous nation, is a key U.S. ally in its battle against al-Qaeda in the region. Ethiopian troops in December invaded Somalia for the second time in four years to join the battle against al-Shabaab, al-Qaeda’s Somalia affiliate.
The federal parliament, which has only one opposition lawmaker out of 547, is expected to swear in Hailemariam on Oct. 8, Bereket said.
At Meles’s funeral on Sept. 2, Hailemariam vowed to continue with his state-led development model that channeled loans, aid, investment and domestic revenue into infrastructure, industry and public services. The result was growth that averaged 10 percent in the past eight years, according to the government.
Human-rights groups criticized the government for cracking down on civil liberties and introducing anti-terrorism laws in 2009 that have been used to jail opposition politicians and journalists.
The EPRDF is a coalition of four parties representing the Amhara people, the Oromo, the Tigray and a collection of southern groups. Meles was leader of the Tigray People’s Liberation Front, which led the ouster of a military junta in 1991, while Hailemariam hails from the southern bloc. His deputy is from the Amhara National Democratic Movement.
The EPRDF’s council, which has 45 representatives from each bloc, chose Meles’s successor from the 36-member executive committee of the party. Ethiopia’s next parliamentary elections are scheduled for 2015.
---
To contact the reporter on this story: William Davison in Addis Ababa at wdavison3@bloomberg.net