Tuesday, November 19, 2013

[Must Watch Full Video] Who Will Forget These Ethiopians Voices From Sau...

በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው መከራ፥ ስቃይ፥ እንግልት፥ ድብደባ፥ እስራት፥ ግድድያ፥ እና ስደት ገደቡን አልፏል፥፥ ይሁን እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ይሄንን ሁሉ በደልእያየን እንዳላየን፥ በወገን ላይ በሚደርስ በደል ከንፈር ከመምጠጥ ያለፈ መንም አለመቆርቆራችንለምንድን ነው?

ሁላችንም እንኳን በወገን ላይ ለሚደርስ መከራ አደለም በራሳችንም ላይ ለሚደርስ መከራ ለበጎነው ብለን ከማለፍ ውጪ ፈቀቅ ያለ የተግባር ስራ ማረግ አለመቻላችን ከማሳዘን አልፎ አሳፋሪ ሰዎች እየሆንን መተናል፥፥

በተለይ በውጭ ሃገር የምንኖር ኢትዮጵያውያን በምንኖርባቸው አገራት ያለውን ለሰው ልጅ የሚሰጠውን ክብር እያየን፥ የሰው ልጅ የነፃነት መብት፥ የመናገር መብት እያየን እንኳን ይህ መብት ለኛ ለኢትዮጵያውያን እንደማይገባን ያህል ማሰባችን ያስገርማል፥፥

በቃ ህልማችን ሁሉ ውጭ ሃገር መተን የሰው አገር ባሪያ ሆኖ ለመቅረት የወሰንን ይመስላል፥፥ 

የሚገርመው ነገር ግን በአረብ ሃገር በኢውሮፕ እንዲሁም በአሜሪካም ጭምር ከሰው በታች ሆነን መኖራችን ነው፥፥

እንነሳ፥

እንነሳ፥

እንነሳ፥!