Tuesday, July 15, 2014

ቅን መሆን ካልቻልክ ፤ ቅንቅን ከመሆን ተቆጠብ !! ካልሆነ ዋጋ ትከፍላለህ ,,,

ቅን መሆን ካልቻልክ ፤ ቅንቅን ከመሆን ተቆጠብ !!
ካልሆነ ዋጋ ትከፍላለህ ,,, የሚለው አባባል በደንብ መስተዋል ያለበት ነጥብ አለው፣ ተመችቶኛል፥

በአሁኑ ሰአት አሸባሪውን የወያኔ መንግስት ለመጣል በኢትዮጵያ አንድነት፥ እኩልነት፥ ፍትህ፥ ዲሞክራሲ እና ነፃነት ስም ላለፉት 23 ምናምን አመታት፥ ምናልባትም ከዛ በላይ በአንድነት ስም የሚታገሉ፥ ወይም ለኢትዮጵያ ህዝብ እንሰራለን የሚሉ በጣም ብዙ ከብዙም ብዙ የፖለቲካ ድርጅቶች እንዳሉ ይታወቃል፥

ይሁን እንጂ አላማቸው ለሃገራችንና ለወገናችን ከሆነ፥ ወያኔን አባረው ስልጣንን ለህዝብ ማስረከብ ከሆነ፥ ለምን አብረው በሚስማሙባቸው ነጥቦች ላይ ብቻ እንኳን ለመስራት ተሳናቸው፥ ?

እንደውም አሁን አሁን በስሜ እየነገዱ ሁሉ ያለ ነው የሚመስለኝ፥ ወይንም በቃ ለሆቢ ይመስላል፥

ሌላው አስጊው ነገር ደሞ ትንሽ ማህበረሰብ ወስጥ ሁሉንም አቻችሎና ተስማምቶ መስራት ሳይቻል፥ የሚፈለገው ስልጣንስ ቢመጣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል መገመት አያስቸግርም፥፥

ስለዚህ ምን መደረግ አለበት?

በአንድነት ስም ተደራጅተው፥ በኢትዮጵያ ስም ተደራጅተው ግን እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ፥ አንዱ ያንዱን ስራ ለማበላሸት እየታገለ፥ / ወይም በፖለቲካ ቋንቋ እየተጠላለፈ/  እስከመቼ.....

መሮናል....መሮናል......መሮናል.....በቃ....በቃ......በቃ......

በሃገር ቤትም ሆነ በውጭ ተደራጅተው ያሉ አካላቶች እንደ ኢሳት ያሉ የህዝብ ሚዲያዎች ላይ መተው ወይንም ስብሰባ መድረክ ላይ ቁጭ ብለው እራሳቸውን፥ አላማቸውን / ምን ሊያደርጉልን እንዳሰቡ/፥ ይንገሩን፥ ከዛ ደሞ በአንድነት ተቀራርበው ሰርተው ያሳዩን፥

ይህ ነገር ከዚህ በኋላ ግድ ነው፥፥ አይ አይሆንም እኔ ብቻዬን ነው የምሰራው፥ ደስ ሲለኝ ብቻ እዛ የፈረደበት ዌብሳይት ላይ ወይንም ብሎግ ላይ መግለጫ ብቻ ነው የማወጣው የሚሉ ካሉ፥ በሃገር ስም የሚቀልዱ ካሉ፥ እነሱም ከወያኔ እኩል ግዜው ሲደርስ ተጠያቂ መሆናቸው አይቀርም፥

በቃን ወያኔም ሆነ 80 የተቃዋሚ ድርጅት መሮናል!

Meleket Radio ቆይታ ከከፍተኛ አሰልጣኝና አብራሪ ካፖቴን ተሾመ ተንኮሉ ጋር