Monday, August 26, 2013

የወያኔ የሰብአዊ መብት ረገጣና የኖርዎይ ፖሊሲ በኢትዮጵያ

የወያኔ የሰብአዊ መብት ረገጣና የኖርዎይ ፖሊሲ በኢትዮጵያ
መስከረም 26፥2013 በ NORAD ኢንፎርሜሽን ሴንተር

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ሃገራት ላይ አምባሳደር ሆኖ መሾም ቀላል አይደለም አክለውም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ ሲገልፁት መርዘኛ፥ በማለት ነበር የተናገሩት ከሰላምታቸው  በመቀጠል ንግግራቸውን የጀመሩት የኖርዎይ አምባሳደር በኢትዮጵያ ኦድ-ኢንገ ክቫልሃይምOdd-Inge Kvalheim / ዛሬ ኦገስት 26፥ 2013 NURAD ባዘጋጀው ክፍት የውይይት መድረክ ላይ ነበር፥፥

በውይይት መድረኩ ላይ ከተገኙት አብዛኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ነድፈው ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተው አስተያየትና ጥያቄዎችን አንስተዋል፥፥

ኑራድ / NURAD/ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስር ያለ ተቋም ሲሆን የኖርዎይ መንግስት ለተለያዩ ሃገራት ለልማት የሚለግሳቸውን የእርዳታ ገንዘቦች ለትክክለኛው አላማና ግብ በጥራት እንዲደርስ ለማስቻል የተለያዩ የምክር አገልግሎቶች የሚሰጥ ተቋም ነው፥፥
ኦድ-ኢንገ የኖርዎይ አምባሳደር ሆነው ከተሾሙ ሶስት አመት ሞልቷቸዋል፥፥ 

በአብዛኛው ከንግግራቸው ለመረዳት እንደሞከርኩት በኢትዮጵያ ውስጥ እየተገነቡ ባሉት ህንፃዎች በመማርከዋቸው የተነሳ በወያኔ እየተፈፀመ ያለው በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው የሰብአዊ መብት ረገጣን ማሰብም አይፈልጉም፥፥ ለነገሩ ቢያስቡስ ምን ያመጣሉ፥፥ እውናታው ከተወሰነ አመት በፊት የወያኔ መንግስት በ NGO ስም ገብታችሁ ፖለቲካ ትፈተፍታላቺሁ ብሎ የኖርዎይ ዲፕሎማቶችን ያባረራቸው ጊዜ ትልቅ አጀንዳ አርገውት ነበር፥፥ በቃ ያንን ስህተታቸውን አይለመደንም ብለው ተመልሰው ከገቡ በኋላ ግን በተደጋጋሚ በወያኔ መንግስት ላይ ከተለያየ አለም እንዲሁም እዚሁ በኖርዎይ ለሚቀርቡ ወቀሳዎች ብዙም ትኩረት አልሰጡትም፥፥

በስብሰባው ላይም ለአምባሳደር ከተለያዩ ኦርጋናይዜሽኖች ከመጡ ግለሰቦች እንዲሁም ከኢትዮጵያውያን በርከት ያሉ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ነበር፥፥ ከጥያቄዎቹም መካከል በጥቂቱ፥



  • ንም እንኳን ኢትዮጵያ በትልቅ የእድገት ጎዳና ላይ ናት ብትልሙም የሚሰደደው ዜጋ ብዛት እያጨመረ ነው
  • የወያኔ መንግስት በተለያየዩ ጊዜያት በሰብአዊ መብት ረገጣ እየተከሰሰ ነው፥
  • ዜጎች ያለአግባብ ከገዛ መሬታቸው እየተፈናቀሉ መሬታቸው ለውጭ ባለሃብቶች እየተቸበቸበ ነው፥
  • ጋዜጠኞችና ደራሲዎች ሃሳባቸውን በመግለፃቸው ብቻ ወደእስር በት እየተጣሉ ነው
  •  አሁን የፊታችን መስከረም በሚደረገው ምርጫ ላይ ከተሸነፋቺሁና የቀኝ  ፓርቲው ማለትም HØYERE ካሸነፈ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው እርዳታ የሰብአዊ መብት አጠባበቅ እስካልተሻሻለ ድረስ እንደሚያቋርጥ ይናገራል፥ ይህ ከሆነ ምን ታደርጋላችሁ፥
  • የታችኛውን የህብረተሰብ ክፍል ይደርሳሉ ተብሎ የታመነባቸው የውጭ NGO ዎች በተጣለባቸው የመንግስት ገደብ ምክንያት ሊሰሩ አለመቻላቸው፥
  • መንግስት በሃይማኖት ተቋማት ላይ ጣልቃ በመግባቱና ዜጎች ተቃውሟቸውን ሰላማዊ መንገድ በማሰማታቸው ብቻ ግድያ፥ እስራትና ድብደባ እየተፈፀመባቸው ነው፥
  • በኢትዮጵያ ውስጥ ሆሞሴክሽዋል በሆኑ ዘጎች መብት ላይ ምን እየእየሰራቺሁ ነው የሚሉና ግርዛትን ለመከላከል ምን እየሰራቺሁ ነው የሚሉና ስለአየር ብክለትን በተመለከተ በርከት ያሉ ጥያቄዎች የተሰነዘረላቸው ሲሆን


እሳቸውም በአብዛኛው የመልስ ትኩረታቸውን ያረጉትና ለማብራራት እንደሞከሩት ኖርዎይ በአሁኑ ጊዜ ቅድሚያ ሰጥታ እየሰራች ያለችው
  • ሴቶችና ህፃናት እኩልነትና መብቶቻቸው ዙሪያ በተለይም ግርዛትን በተመለከተ
  • የአየርና የአካባቢ ብክለትንና እየፈጠረ ያለውን እድገት ለመከላከል ኢትዮጵያ፥ ኖርዎይና ኢንግላንድ በ2011 ዱርባን ላይ የተፈራረሙትን የሶስትዮሽ የስራ ስምምነት ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በተግባር ማስፈፀም
  •  የኢኮኖሚ እድገትን በተመለከተና  በመጨረሻም 
  • ዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ዙሪያ ከዩናይትድ ኔሽን የሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ኮሚሽን ጋር በመሆን ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በመሰራት ላይ መሆናቸውን ገልፀው አልፈዋል፥፥
ወደ መጀመርያው ጥያቄ ልመለስና ኢትዮጵያ በትልቅ የእድገት ጎዳና ላይ ናት ብትልሙም የሚሰደደው ዜጋ ብዛት እያጨመረ ነው በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ኤርትራን ጨምሮ ወደ ተለያዩ የአረብ ሃገራት እየተሰደዱ በዛም አልያም በመንገድ ላይ ወይንም እዛም ከደረሱ በኋላ ህይወታቸውን እያጡ ነው እድገትና ሰላም ካለ ለምን ይህ ሆነ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ በተቃዋሚዎች በኩል የተጋነነ ነገር እንደሚወራና የተባለው ነገርም መረጃው እንደሌላቸው ገልፀው ተቃዋሚዎች የሚሰራውን ሰራ ሁሉ በበጎ አይመለከቱትም እነሱም አንድ ላይ ቁጭ ብለው መወያየት አይችሉም ለምሳሌ በኖርዎይ ምንም እንኳን አነስተኛ ቁጥር ያለው ኢትዮጵያዊ ቢኖርም ከ13 እስከ 15 የሚጠጉ የተለያዩ ድርጅቶች አሉ ብለዋል፥፥ 

አባባሉ እውነታነት ያለው ነጥብ የሚያሰጣቸው አባባል ቢሆንም ለጥያቄው ግን መልስ አልነበረም፥፥ ለማንኛውም እኛ ለጠየቅናቸው ጥያቄዎች በቂና አጥጋቢ መልስ አጊንተናል ብለን ባናምንም ያገኘነውን አጋጣሚ በመጠቀም ጥያቄዎቻችንንና ሃሳቦቻችንን ለመግለፅ ችለናል፥፥

ኢትዮጰያ በክብር ለዘላለም ትኑር!



ጌዲዮን