Wednesday, May 29, 2013

ሰማያዊ ፓርቲ ወያኔዎችን ባነነባቸው

ሰማያዊ ቀለም ድሮም ይመቸኛል፥ ይገርማል አሁን ደሞ በፓርቲ መጣብኝ፥ ይሁን እንጂ አሁንም ተመችቶኛል ደልቶኛል፥፥ ለዚሁም ደሞ ማረጋገጫው አሁን በግንቦት 25,2013 የጠሩትን የሰላማዊ ሰልፍ በጣም ስለምደግፈው ነው፥፥ አበጠም ፈነዳም ሰማያዊ ፓርቲዎች የሞከሩትን ሙከራ እስከዛሬ ድረስ አለን በሰላማዊ ትግል የኢትዮጵያ ህዝብን ጥያቄ እናስመልሳለን ወያኔን እናስወግዳለን ሲሉ የነበሩት ሰዎች ሁሉ እንኳን ሊሞክሩት አደለም አስበውትም አያቁም ነበር፥፥ 

አሁን ዋናው ነገር የትም ግዥው ቅምቀማውን አምጪው ስለሆነ ሁሉም የተቃዋሚ ፓርቲዎች ወያኔን በሰላማዊ መንገድ እናስወግዳለን የሚሉ ሁሉ ከሰማያዊ ፓርቲ ጎን ሆነው የኢትዮጵያ ህዝብን ለ22 አመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎች እንደተወካይ ማሰማት ግድ ይላቸዋል፥፥ ይህ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ 1ሚሊዮን ሰው፥ 100 ሺ ሰው ወይም 100 ሰው መጣ ሳይሆን ውጤት ተገኘበትም አልተገኘበትም ወያኔ ግን እራሱ ላወጣው ህገመንግስት ተገዢ መሆን ግዴታው እንደሆነ ትምርት ይሰጣል ብዬ አምናለው፥፥

ሰማያዊ ፓርቲዎች በርቱ፥ ጀግኖች ናችሁ፥ እግዚአብሄር ከናንተጋር ይሁን፥፥ ከወሬኛ ይሰውራችው፥ እየሰራችው ያላችሁት ነገር ደስ ይላል፥ በአሁን ሰአት ብዙ አይነት ጠቃሚ እና እንዲሁም የማይረባ ወሬ ልትሰሙ ትችላላችው፥ ጠቃሚውን ብቻ ይዛችው የማይረባውን ደሞ እርሱት፥፥ 

ጌዲዮን 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!