መቼም ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት በቀን የተለያዩ ሰበር ዜናዎች ከሚለቀቁባቸው አገሮች ውስጥ አንደኛ
እንደምትሆን እርግጠኛ ስለሆንኩ ማንም ሊከራከረኝ አይችልም፥፥ በአሁኑ ሰአት ወያኔ ወንጀለኛ ናችው እያለ የሚያስራቸው፣የሚገድላቸው፥
የሚያፈናቅላቸው፥ የሚያሰድዳቸው ብቻ ምን አለፋችው ይደክማል፥፥
በአሁኑ ሰአት ኢትዮጵያ ውስጥ ወያኔ መሆን ብቻ ነው ወንጀለኛ የማያስብለው፥ ከዛ ውጭ አርፈህ
መቀመጥ ግድ ይልሃል፥ ወይም ደሞ ወደፈረደበት ስደት መንገድ አቅንቶ በየበረሃው መሞት አልያም ደሞ እድል ከቀና መናገር የሚቻልበት
አገር መቶ እንደፈረደብን መጮህ፥፥
እኔ እንደገመገምኩት ከሆነ ወያኔ ጨካኝ ውሸታም ገዳይ የሆነ መንግስት ነው፥ የዚህ ውጤቱ ደሞ
የራስን ሞት ማጣደፍ ሊባል ይችላል፥፥
ሰሞኑን አንድ የገረመኝና የከነከነኝ ነገር ቢኖር የወያኔ ዘጠነኛ ጉባዔ ላይ በተደረገው የአመራር
ለውጥ የድርጅቱ ዋና ዋና ቀንደኛ የኢትዮጵያ ጠላት የተባሉትን እንዲሁም የወያኔ አውራዎች ከስልጣናቸው መነሳታቸው ምናልባት እንደነ
ታምራት ላይኔ እና ስዬ አብርሃ እንደፈለጉ ሃገራችንን ሲገድሉ ቆይተው አሁን ደሞ እንደለመዱት ወደውጭ ሃገር ለስራ በመምጣት ተመሳስለው
ለመኖር ፈለጉ እንዴ ብዬ አሰብኩ፥፥ለነገሩ እንተዋወቅ የለ የኢትዮጰያ ህዝብ የዋህ ይቅር ባይ አይደል፣ ምን ችግር አለ፥
አሁን እኮ ወያኔዎች እንኳን የኢትዮጵያ ህዝብ አደለም እርስ በርሳቸውም እንደተሰለቻቹ እያወቁት
መተዋል፥ መሰለቻቸት ከመጣ ደሞ አቤት ለሊቱም አይነጋ፥ ለሊቱ አልነጋም ማለት ደሞ፥
ወየውልሽ አዳሜ
From Gedion