Friday, October 26, 2012

እራሱን ያልሆነው ጠ/ሚንስትር


ጌዲዮን ደሳለኝ ከኖርዎይ
ለሁለት  አስርተ አመታት በኢትዮጲያና  በህዝቦቿ ላይ ነግሶ በማን አለብኝነት አድራጊ ፈጣሪ ሆኖ በሁሉም ያገሪቱ አቅጣጫዎች ሰላማዊውን ህዝብ ለሞትና ለስደት እንዲሁም ለእስር ሲዳርግ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ በፈፀመው ግፍና ሰቆቃ ለምድራዊ ፍርድ ሳይበቃ ይችን አለም ሲሰናበታት የብዙዎቻችን ነፃነት ናፋቂዎች ተስፋ ቢለመልምም ስርዓቱ ካለው እኩይ ተፈጥሯዊ  ባህሪ አንፃር የናፈቅነውንና የተመኘነውን ነፃነትም ሆነ ለውጥ ሳይመጣ እነሆ ሌሎች ንፁሃን ሲገደሉና ሲሰደዱ እንዲሁም ሲታሰሩ አየን ሰማን፡፡
ለብዙሃን ዜጎች ህይወት መጥፋት፣ መሰደድና በየእስር ቤቱ መታጎር ተጠያቂ የሆነው አምባገነኑ የወያኔ ቡድን እንዲሁም ስርዓቱ  በተለይ ሃገር ሲያፈርሱ፣ ሲመዘብሩና ደሃውን የህብረተሰብ ክፍል ሲየፈናቅሉና በችጋር ሲቆሉ የነበሩት የህወሃት መስራቾች በዘፈቀደ ባገኙት አጋጣሚ እዚህ ምስኪን ህዝብ ላይ አፋቸውን ያላቀቁበትና የተዘባበቱበት አውሬው መሪያቸው ከሞተ በሗላ መሆኑ አንድም ሰውየው በህዝብ ላይ ብቻ ሳይሆን ጋሻ ጃግሬዎቹም ጭምር  ስብህናቸውን ሸጠው ሲረገጡ መኖራቸውን የሚያሳይ ሲሆን፡ አልያም ህልውናቸውን በነበረበት ሁኔታ ለማቆየት በህዝብ ላይ የፍርሃት ድባብ ለማስፈን የእውር ድንብራቸውን  ዘርን ከዘር፣ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት በነሱ መልካም ፈቃድ  የስልጣን ዝውውር የተደረገ ይመስል ስልጣን ከአማራና ከኦርቶዶክስ እጅ አውጣን እያሉ ውሃ የማይቋጥር ተራ ዲስኩር በአስተሳሰብ ከነሱ ቀድሞ ዘርና እምነት ሳይለየው በአንድነት ለጠላቸው ህዝብ ሲነግሩት ሰንብተዋል፡፡
ጥቂት የማይባል የህብረተሰብ ክፍል ለዝች ዘመናትን በግፍና በመከራ ላሳለፈ ሃገርና ህዝብ የመጣል ተብሎ በታሰበው ወይም በመጣው አዲሱ መሪ ላይ ጭላንጭል ተስፋ ሰንቆ ቢቆይም  ተስፋ አሰቆራጭ ሁኔታ የተፈጠረው ብዙም ግዜ ሳይፈጅ መሆኑ ተስፋ አድርጎ የነበረውን ተስፈኛ አሁንም የመከራው ቀንበር መፈታት ሳይሁን አለመላላቱን  ያየነው አዲሱ  ጠ/ሚንስትር  ሃ/ማርያም ደሳለኝ ከሀ እስከ ፐ የሟች  ቅጂ መሆናቸው እየተስተዋለ ሲመጣ ነው፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ ሟች አምባገነን መለስ ዜናዊ በዙሪያው የሚሰበስባቸውና ወደ ስልጣን የሚያስጠጋቸው ሰዎች ምን አይነት አመለካከትና ስብእና ወይም ሀገራዊም ሆነ ህዝባዊ ስሜት አላቸው ? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ሊቅ ወይም ነብይ መሆን የሚጠበቅብን አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ሰውየው(ሟች) ይችን ሃገር በገዛበት ሁለት አስርተ የግፍና የመከራ ዘመን ውስጥ በራሳቸው የሚተማመኑትን፣ በሃሳብ ደረጃ እሱን የሚሞግቱትን በተለይ ለሃገርና ለህዝብ የሚጠቅም ፅንሰ ሃሳብ የሚያንፀባርቁትን የሃገር ሃብት ምሁራን ሲገድል፣ ሲገፋና ሲያሳድድ በግፍ ሲያስር የስልጣን ዘመኑን ማሳለፉ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ በአመለካከት ከሱ የተለዩትን አብረውት በትግል ሜዳ የነበሩትንም ሁሉ  ሳይቀሩ  ሲያሶግድ፣ ሲያስርና ሲያሳድድ መኖሩ  በህይወት ያሉ የቀድሞ የህውሃት ሰዎች ምስክር ናቸው፡፡ ይህንን ከተረዳን አቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝ  በመለስ ዜናዊ ተመርጠው  እንዴት እዚህ ደረሱ የሚለውን ለማወቅ ከላይ እንደጠቀስኩት ነብይ መሆን አይጠይቅም፡፡
በሁለተኛ ደረጃ አቶ ሃ/ማርያም በአለም አቀፍ ማህበረሰብ ተፅእኖም  ይሁን ወያኔ የህዝብ ይሁንታ ለማግኘት ቁልፍ የሆኑ የስልጣን ቦታዎችን  ይዞ ከፊት አስቀድሞ መንበረ ስልጣኑን ቢሰጣቸውም  ምንም  የመወሰን አቅም  የሌላቸው ወያኔ ለሽፋን ያስቀመጣቸው መሆናቸውን ያየንባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው፡፡የሳቸውም በራስ ያለመተማመን መንፈስና የስብእናችው ጉዳይ ታክሎበት በይዘትም ሆነ በፅንሰ ሃሳብ የግፈኛውን የመለስ ቅኝት መሆናችው እያየን ያለነው ገና በጠዋቱ የስልጣን ግዜያቸው ነው፡፡ የእሳቸው እራሳቸውን ያለመሆን ችግር አንድም እርምጃ ወይም ውሳኔ ለይስሙላ በተሰጣቸው ስልጣን እንደማይፈፅሙ የሚያሳየን  የህዝብና የሃገር ሃብትን ንብረትን በመመዝበር በምትታወቀው በሟች ባለቤት አዜብ መስፍን  ከቤተ-መንግስት  መውጣት አሻፈረኝ በማለቷ ስልጣናቸውን በይፋ ከተቀበሉ በሗላ ከወር በላይ መኖሪያቸውን ተረክበው በቤተ-መንግስት አለመግባታቸው ሰውየው ሳይሆኑ ለሃያ አንድ አመታት  ኢትዮጲያንና ህዝቧን ያስነቡና ያሰቃዩ የነበሩት የህውሃት ሰዎች መዘውርን እንደጨበጡት አንዱ ማሳያ ነው፡፡
የአቶ ሃ/ማርያም ደሳለኝን  ሹመት በተመለከተ በተለያየ ጊዜ ብዙ ተብሏል፡፡ አብዛኛው እኔን ጨምሮ ከላይ  በጠቀስኳቸው ጉዳዮችና ከዚህ አፋኝና  አምባገነን ስርዓት  ተፈጥሯዊ ባህሪ  አንፃር  ሰውየው የግፈኛውና የአምባገነኑ መለስ ቅጂ (ግልባጭ) ናቸው፡፡  ስርዓቱ እስካልተወገደ ድረስ ለውጥ  መጠበቅ ከእባብ እንቁላል እርግብ እንደመጠበቅ ነው ስንል  በጣም ጥቂት የዋሆች ግን ጊዜ ይሰጣቸው ይሉ እንደነበር  ይታወሳል፡፡ብርቅዬው ገጣሚ ሄኖክ የሺጥላ ለማይነጥፈው ብእሩ ምስጋና የግባውና ለ አቶ ሃ/ማርያም  ጊዜ ይሰጣቸው ለሚሉ ተስፈኞች ግጥም ፅፎ ነበር፡፡ እሺ ጊዜ ይሰጥ ግን ስንት ገለው ይብቃቸው፣ ኮታቸው ስንት ነው  ስርዓቱ እያለ  መግደል አያቆሙምና ደግሞ እሳቸው ስንት እስኪገሉ እንያቸው  ነው ያለው ገጣሚው፡፡ እና ይህው ብዙም አላለፉንም የስልጣን ጊዜያቸው ወራት ሳያስቆጥር  አስፈፅማለሁ ያሉትን  የሟች አለቃቸውን እቅድ  በደቡብ ወሎ በደጋንና ገርባ ከተሞዎች መብታቸውን በሰላማዊ መንገድ  የጠየቁ  ንጹሃን ዜጎችን በጠራራ ፀሃይ በመግደልና በማሰር የሟች አለቃችውን  እቅድ በመተግበር  በንጹሃን ደም  ታጠቡ፡፡
ሰውየው ኢትዮጲያንና ህዝቧን የሚመሩት  ከአለቃቸው በውርስ ባገኙት የሳቸው ባልሆን  ባህሪ ብቻ ሳይሆን ይችን ሃገር መዝብረው በደለቡና በሰቡ የህውሃት ሰዎች በርቀት መቆጣጠሪይ ስለሆነ  ከህዝብ ሳይሆን  ከነኚሁ የሃገርና የህዝብ ጠላቶች  ክብርና ሞገስ  ለማግኘት እንደ ሟች አለቃቸው  ሆዳምና ከራሱ ባለፈ ስንዝር  የማያስብ  ጥርቅም በሞላበት ፓርላማ ተብይ ውስጥ በሙት መንፈስ  እየተመሩ  መኮረጅ የቻሉትን  ያህል  ሲተውኑ፣  ተልኳቸውን በድል ለመወጣት ሲወራጩና  ሲሳደቡ፣ እንዲሁም ህዝብ  ክብር የሚሰጣቸውን የህሊና እስረኞችንና የነፃነት ታጋዮችን  ሲዘልፉ፣ ከቃላት አጠቃቀምና አስተያየት ጀምሮ የሳችው ባልሆነ ስብእና  የሚያደርጉት ትእይንት  በሳችው ደረጃ ካለ   ከተማረና  ከዚህ ዘመን ስልጡን ሰው የሚጠበቅ አይደለም፡፡
 ላይ ላዩን ቅልም ዱባ ይመሰላል እንዲሉ  የአቶ ሃ/ማርያም ስልጣን ሳየቀመጡበት መነቃነቅ ጀምሯል፡፡ ሟችቹ መለስ ትቶት ሄደው ዘርፈ ብዙ ችግር ወትሮም  ቅንነት የጎደላቸውን አዲሱን ጠ/ሚንስትርም  ሆኑ የስርዓቱን አውራ  ገዳዮች  ይንጣቸው የዟል፡፡ ከመጀመሪያ ጀምሮ  በአለቃቸው  ሞት ልባቸው መራድ  የጀመረው  የወያኔ  ቱባ ባለስልጣናት  ሊፈጠር  ይችላል ብለው ያሰቡትን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማፈንና  በህዝቡም ላይ ፍርሃት ለማንገስ  ለአዲሱ ጠ/ሚንስትር እውቅና ከመስጠታቸው በፊት ከስርዓት ውጪ በሆነ መንገድ  በአብዛኛው ከህውሃት ለሆኑት የተሰጠው ወታደራዊ ሹመት(የማእረግ  እድገት) በውስጣቸው ያልሰከነ ነገር ለመኖሩ አመላካች ነው፡፡ ከዚም ባለፈ  አቶ ሃ/ማርያም  እስከ አሁን ካቢኔያቸውን አለማሳወቃቸውና  ሌሎችም በሰርዓቱ ላይ የሚታየው ሰፋፊ ክፍተት፣ እንዲሁም ገዢው ቡድን እንደ አሻንጉሊት  የሚጫወትባችው  አጋር  የብሄር ድርጅቶች ውስጥ  የሚታየው መተራመስ  ስርዓቱ  በደመነፍስ  እየተውተረተረ  እንዳለ የሚያሳይ ነው፡፡
ይህንን ስርዓት  ለመጣል  በቅን ልቦና  በመደማመጥና ለጋራ ጥቅም  በአንድነት  ከታገልን በትንሽ መስዋትነት ሃገራችንንና  ህዝባችንን ነፃ ማውጣት አይገደንም፡፡
ድል  ለኢትዮጲያ   ህዝብ !!  ሞት ለወያኔና  ለሆዳሞች!!!!

Ethiopian Asylum Seekers in Norway protest in Oslo against the Ethiopian Dictatorial Regime and the Norwegian Asylum policy.


By Gedion Dessalgne


Ethiopian Asylum Seekers in Norway demonstrate in Oslo against the Ethiopian dictatorial regime 18. October 2012. Around 400 people gathered first in Oslo central station and we went to the Norwegian parliament by showing our problem with deferent slogans.

Gedion program leder
We Ethiopian asylum seekers in Norway who have been lived for a long until 17 years without resident permit, but have been working for many years and paid taxes, politicaly  active  by joining opposition parties, protesting against the Ethiopian dictatorial regime through all this years.

Us we all know Norway have signed a deportation agreement with the Ethiopian regime to deport rejected Ethiopian asylum seekers in Norway who have been lived for so many years, among us people who have been living for 17 years, people who have established family, have children, people who are suffering mental illnesses and so on.

We Ethiopians have fled from our country because of the TPLF regime that has been in power for more than 22 years. We have suffered a lot, and experienced torture, prison, and discriminate in our own country.

Since Norway has signed the deportation agreement in January 26, 2012 with Ethiopian dictatorial regime, we are suffering a lot.

Now the dictator Meles has gone for good, but TPLF is still leading our country. The new PM Hailemariam Dessalgn told on his first speech that, there will not be any policy change and he confirmed that opposition political parties, jourlalists, and activists who are in prison are terrorists.

Tousends of people are still in prison without any hope of change.

To see the deportation agreement between Norway and the Ethiopian dictatorial regime.



Gedion Dessalgne from Norway