Saturday, January 16, 2016

Welkait Tegede has always been indigenous Amara's Land not Tigray's.

ወልቃይት አምርሯል “ትግሬ አይደለንም፣ አማራ ነን” ብሏል


ህወሓት (ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ) የአማራ ብሄረሰብ ተወላጆች የሚኖሩበትን የወልቃይት-ጠገዴን ለም መሬት ወደ ትግራይ ክልል በጉልበት ከጠቀለለ ጀምሮ የወልቃይት ነዋሪ የአማራ ብሄረሰብ አባላትን በግድ ትግሬ የማድረግ ዘመቻ ሲያከናውን ኖርዋል። በርካታ ከህወሓት ሰራዊት በጡረታ የተገለሉ የትግራይ ተወላጆች በወልቃይት ኑሮ እንዲመሰርቱ ተደርጓል። (ይህ የሚደረገው በወልቃይት የትግራይ ተወላጆችን ቁጥር ለማብዛት ነው)።
በወልቃይት ህፃናት በግድ ትግርኛ ቋንቋን ብቻ እንዲናገሩ ይገደዳሉ፣ የወልቃይት ሴቶች በግድ የትግራይ ተወላጆችን እንዲያገቡ ይገደዳሉ፣ የወልቃይት ሴቶች ከሀገራቸው የወልቃይት ወንድ ጋር ጋብቻ እንዳይፈጽሙ ይደረጋል (ጋብቻ የፈጸሙትም ትዳራቸውን እንዲያፈርሱ ይደረጋል)፣ የወልቃይት ሴቶች ከሀገራቸው ወንዶች ጋር የፈጸሙትን ትዳር አናፈርስም ካሉ ለህክምና ወደ ጤና ጣብያዎች በሚሄዱበት ወቅት ልጅ እንዳይወልዱ (መሀን) የሚያደርግ መድሃኒት እንዲወጉ ይደረጋል። እነዚህን ኢሰብአዊ ድርጊቶች የተቃወሙና ህወሓቶች ያልወደዷቸው በርካታ የወልቃይት-ጠገዴ አማሮች በግፍ ተገድለዋል፣ አንዳንዶችም ጠመንጃ አንስተው ህወሓትን ሲፋለሙ ኖረዋል አሁንም ብዛት ያላቸው የወልቃይት አማሮች በአርበኝነት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።
የወልቃይት ነዋሪዎች ይህንን ሁሉ ኢሰብአዊ ድርጊት ተቋቁመው ኖረው ነው አሁን በቃ እያሉ ያሉት።
የወልቃይት ነዋሪዎች በተቀናጀ መልኩ ወደ አማራ ክልል ተወካዮቻቸውን በመላክ ህዝብ በተሰበሰበበት “እኛ ወልቃይቶች አማሮች ነን፣ ወልቃይትም በአማራ ክልል ስር መሆን አለበት፣ ወልቃይት-ጠገዴ በትግራይ ክልል ስር እንዲሆን የተደረገው አላግባብ ነው፣ ስለዚህም የአማራ ክልል ባለስልጣኖች እና የአማራ ህዝብ ችግራችንን ተረድተው ወልቃይት በአማራ ክልል ስር እንዲሆን እርዳታችሁን እንፈልጋለን” ሲሉ ደጋግመው ተናገሩ።
በህወሓት ተላላኪነት የሚታወቁት የብአዴን ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ሰሞኑን ከህወሓት የተሰጣቸውን ቀጭን ትዕዛዝ ይዘው ወደ ወልቃይት አምርተዋል፣ ባለስልጣናቱ ዋነኛ አላማቸው አድርገው የያዙት የወልቃይት ነዋሪዎችን በማግባባትና ይህም አልሰራ ሲላቸው በማስፈራራት በግድ ትግሬዎች ናችሁ አምናችሁ ተቀበሉ የሚል መልእክት አዘል ህወሓታዊ ትእዛዝን ማስፈጸም ነው።
አቶ ግደይ የሚባለው የዳንሻ ወረዳ አስተዳዳሪ የወልቃይት አማሮችን አንገት ለማስደፋት ይመስላል በመሀይም አንደበቱ እንዲህ ሲል ተደምጧል፣
“የወልቃይት-ጠገዴ ወጣቶች አማርኛ ቋንቋን የተማራችሁት ከአዝማሪ ነዉ፣ እናንተ ትግሬዎች ናችሁ…”
የወልቃይት-ጠገዴ ነዋሪዎች በተለይም ወጣቶቹ ግን ካነሷቸው ጥያቄዎች የማፈግፈግ ስሜት አልታየባቸውም። ይልቁንም ዛሬ ጥር 4 ቀን 2008 በይደር ተይዞ ቆይቶ በዳንሻ የተደረገው ስብሰባ ወጣቶቹ “የወረዳውም ሆነ የከተማው አስተዳዳሪና ባለስልጣኖች በተደጋጋሚ ማንነታችንን የሚያንቋሽሹ፣ ወጣቶችን የሚደበድቡ እና የሚያስደበድቡ በመሆናቸው፣ አንዳንዶቹም በግድ ትግሬዎች ናችሁ በማለት ማንነታችን ለመፋቅ ሲሞክሩ የነበሩ በመሆናቸው፣ አልማዝ ገብሬ የተባለች አድርባይ ቤት ለቤት እየዞረች ሴቶችን ‘ትግሬ ነን በሉ’ በማለት ስትቀሰቅስ የነበረች በመሆኗ… በአጠቃላይ አመራሩ እኛን የመምራት ብቃት ስለሌለው የበላይ አለቆቻችሁ መጥተው ያነጋግሩን”። በማለት ስብሰባው እንዲበተን ሆኗል