Tuesday, November 6, 2012

አላማችን ላይ ሊያደርሱን ያልቻሉ ማጣመሮች

ጌዲዮን ደሳለኝ (ኖርዌይ)

ወደድንም ጠላንም የኢትዮጵያ ሁኔታ ወደአንድ አቅጣጫ እያመራ እንደሆነ እየተከናወነ ያለው እውነታ ይመሰክራል ነገሮች በፍጥነት እየተለወጡ ነው ያለው፣ ትላንት የሰማነውን አዲስ ነገር አጣጥመን ሳንጨርስ ሌላ አዲስ ነገር ይፈጠራል ይህ ደግሞ በአገራችን እየተከናወነ ያለ የለት እለት ክስተት ሆኗል።

የዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ዋናው ምክንያት እኛ ስንጣመር፤ ስንቀናጅና ስንተባበር ትግሉን በዚህ ብቻ በመጨረስ። የተግባር መግቢያው ወቅት እያለፈን እንዳለ ስለተገነዘብኩ ነው። አንዳንዴ እንደውም እኛ ተቃዋሚ የምንባለው የወያኔ ስርአት ተወደቀ የምንጎዳ ይመስል ወደትግል ከመግባትና ከማስገባት፣ ከመታገልና ከማታገል ይልቅ ስንተባበር፣ ስንቀናጅና ስንጣመር ዘመናትን ያስቆጠርን ይመስላል በዚህም ወሳኝ የሆኑ የለውጥ ወቅቶች እያለፉን ይገኛሉ።

ጀግናው የተወደደ አበበ ገላው አቶ መለስ ላይ የኢትዮጵያውያንን ቁጣ ካወረደባቸው በኻላ በደረሰባቸው ታላቅ መቅሰፍት ይኽው ከመድረክ ከጠፉ ሁለት ወራቶች ተቆጠሩ በጀግናው አበበ ገላው የተለኮሰው እሳት ከሳቸው መጥፋት ጋር ተዳምሮ በኢትዮጵያውያን ዘንድ ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴዎች ተጀምረው ነበር አገሬውም ውጭ ያለውም ብሩህ ዘመንን እያየ ለለውጥ ሲነጋገር፣ ሲሰራና ቢንቀሳቀስም ማንም ከጎኑ ቆሞ የሚረዳውና ትግሉን የሚመራለት አካል አላገኘም።

መተባበር፤ መቀናጀትና መጣመር ለትግን ጠቃሚ መሳሪያ እንደሆነ ማንም አይዘነጋውም ነገር ግን ከዚህ በማያያዝም እንደሚባለው መሬት የረገጠ ትግል ስናደርግ ነው እንድምታ፣ ጥቅምና ውጤት የሚኖራው እንጂ ትርጉም የሌለው መተባበር፤ መቀናጀትና መጣመር ወያኔን ግዜ እንዲገዛ ከማድረግና ለሱ እስትንፋስ ከመስጠት በስተቀር የሚፈይደው ፋይዳ የለም።

ስለለውጥ የሚሰብኩና የሚዘምሩ ተቃዋሚዎችና ህብረቶች የሚፈተኑበት ሰአት አሁን ነው። ህዝብ ምሩን፣ አታግሉን፣ ለድል አብቁን፣ ቀንበሩን ከላያችን ላይ አንከባሉልን፣ ከግፍ ከእስራትና ከእንግልት አድኑን እያለ በሚጣራና በሚጮህ ሰአት ተቃቃሚዎች ትላንት ስንጣመር፣ ዛሬም ስንተባበር፣ ነገም ስንቀናጅ በእጃችን ላይ ያሉ ያለቀላቸው የድል ወቅቶች እያመለጡን ይገኛሉ።

መች ጠባችን ከመተባበር፤ ከመቀናጀትና ከመጣመር ጋር ሆነና፣ ጠባችን ከዛወዲያ የት አላችሁ? ከሚለው ጋር ነው እንጂ። ተገናኙ፤ ተነጋገሩ፤ ተጨባበጡ ስንባል እሰይ እልል እንደምንል ሁሉ ከዛ በኻላ ድምጻችሁ ሲጠፋ የደረሳችሁበት ሳናውቅ ስንቀር ወቅቱ እንዳያመልጠን ስለምንሰጋ እንጨነቃለን። ለለውጥ ከዚህ የበለጠና የተመቸ ጊዜ መቼም ሊመጣ እንደማይችል ለመገመት ጠበብት መሆን አያስፈልግም፤ በዚያች አገር የሆነ ነገር ሊወለድ እንዳለ ምልክቶች እየታዩ ነው ግን ጥያቄው አዋላጅ ከየት ይምጣ ነው? ከሌለ ደግሞ የሚወለደው ሊጨነግፍ ይችላል።

ለህብረት፣ ለመጣመር እና ለመቀንቅጀት እንደምንሯሯጥ ሁሉ ትግሉን ከግብ ለማድረስ ምነው ሰነፍን ጎበዝ ይህ ወቅትም እየሮጠ እንደሆነ መገንዘብ አለብን ወያኔ የተንገዳገደውንና የተሰነጠጠቀውን ያህል ተባብረን በአፋጣኝ ግዜ ሳንሰጥ ገፍተን ካልጣልነው በሚያገኘው ትንሽም ግዜና ትንፋሽም ቢሆን ነፍስ ዘርቶና አንሰራርቶ ጭንቅላታችን ላይ ሊቆም ስለሚችል ልንፈጥንና ወደስራ ልንገባና ልናስገባ ያለው ሁኔታ የግድ ይላል።

በመሆኑም ወቅቱ የስራ መሆኑን ተገንዝበን የተባበራችሁ አካላት ሁሉ ለውጥ ፈላጊውን ማህበረሰብ በማስተባበርና በማቀናጀት መሬት ወደረገጠው ትግል ግዜ ሳንወስድ እንድንገባና የወያኔ አገዛዝን እድሜ እንድናሳጠር ወቅታዊውን የህዝብ ጥያቄ ታደምጡ ዘንድ ታሪክና ወቅቱ ያስገድዳል።

ስለዚህ ለተከበራችሁ፣ የተባበራችሁ፣ የተቀናጃችሁ እንዲሁም የተጣመራችሁ አካላት በሙሉ ይህ ጥሪያችን አክብራችሁ ትግሉ በሚጠይቀው በአሁኒቷ ወሳኝ ሰአት እኛን በማስተባበር በመምራት ለድል ታበቁን ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!




Monday, November 5, 2012

11ኛው ሰዐት




በቅርቡ የወጣው አንድ ጥናት እንደሚያመለክተው 40 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ኢሃዲግን በቀጥታ እንደሚቃወሙ 

የገለጸ ሲሆን ሌሎች 10 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የተሻለ የፖለቲካ አማራጭ እስከሌለ ድረስ የአንድነት ፓርቲ 

እንደተመቻቸው አስተያየት ሰተዋል በተያያዘ ጥናትም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተቃዋሚዎችን የሚደግፈው ኢትዮጵያዊ ከግዜ 

ወደግዜ ወደግዜ በጅጉ እየጨመረ ሲሆን ይህ ጥናት ጅቡቲን ጨምሮ በሌሎች የአለም ክፍሎች የሚኖሩ ዲያስፖራዎችን 

እንደሚያጠቃልል ተብራርቷል፥ 

መጪው ዘመን ከነሳነት ሃይሎች ጋር ብሩህ ይሁን፥፥


ይህንን ጥናት የተመለከቱ ጥቂት ፍርፋሪ የ ወያኔ ሆድ አደር ባርያዎች እንቅልፍ ነስቶአቸው እየተቅበዘበዙ ይገኛሉ፥፥




Sunday, November 4, 2012

የመድረክ ሥራ አስፈጻሚን ጨምሮ በሽብርተኝነት ወንጀል የተከሰሱ ዘጠኝ ሰዎች ጥፋተኛ ተባሉ


“ባለቤቴ ከሥራ እንድትወጣ በመደረጓ ልጆቼ ያለገቢ ለመኖር ተገደዋል” የመድረክ ሥራ አስፈጻሚ
በታምሩ ጽጌ
ከሁለት ዓመታት በፊት ጥቅምት 1 ቀን 2002 ዓ.ም. በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት የመድረክ ሥራ አስፈጻሚና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የውጭ ቋንቋ መምህር አቶ በቀለ ገርባና ሌሎች ስምንት ተከሳሾች ጥፋተኛ ተባሉ፡፡ የፌዴራል ዓቃቤ ሕግ ሕጋዊ ፓርቲን (ኦፌዴንና ኦሕኮን) ሽፋን በማድረግ ወጣቶችን በመመልመልና በማሠልጠን በተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት በተፈረጀው የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) በህቡዕ እንዲሠሩ አድርገዋል በሚል ክስ ተመሥርቶባቸው ጥቅምት 22 ቀን 2005 ዓ.ም. የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈባቸው አቶ በቀለ ገርባና አቶ ኦልባና ሌሊሳ ናቸው፡፡ 

ሌሎቹ የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈባቸው ወልቤካ ለሚ፣ አደም ቡሳ፣ ሀዋ ዋቆ፣ መሐመድ መሉ፣ ደረጀ ከተማ፣ አዲሱ ሞክሬና ገልገሎ ጉፋ የተባሉ ግለሰቦች ሲሆኑ፣ የኦነግ አባል በመሆን በተለያዩ ቦታዎች ተማሪዎች እንዲረብሹ፣ ወጣቶችን በመመልመልና ኬንያ ድረስ ወስደው በማሠልጠን በህቡዕ ሲንቀሳቀሱ መገኘታቸውንና ሌሎችንም ድርጊቶች ፈጽመዋል በሚል ዓቃቤ ሕግ የመሠረተባቸውን የሽብርተኝነት ወንጀል ማስተባበል አልቻሉም ተብሎ ነው፡፡ 

ሁሉም ተከሳሾች የተከሰሱበትን የሽብርተኝነት ወንጀል አለመፈጸማቸውን በመከራከር የመከላከያ ምስክሮችም አቅርበው ያሰሙ ቢሆንም፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት ተከሳሾቹ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበባቸውን ክስና ማስረጃ ማስተባበል አለመቻላቸውን በመግለጽ የጥፋተኝነት ፍርድ አስተላልፎባቸዋል፡፡ 

ጥቅምት 22 ቀን 2005 ዓ.ም. የጥፋተኝነት ፍርድ የተላለፈባቸው ዘጠኙም ተከሳሾች የቅጣት ማቅለያ ሐሳብ እንዲያቀርቡ ተጠይቀው ማቅለያ ሐሳብ አቅርበዋል፡፡ አቶ በቀለ ገርባ ባቀረቡት የቅጣት ማቅለያ እንደተናገሩት “ሕይወቴን በሙሉ አድልዎን፣ ኢፍትሐዊነትንና ዘረኝነትን በመቃወም በፈቃዴ ሳይሆን በፈጣሪ ፈቃድ፣ ለኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች መከበር በመታገሌና መስዋዕት በመሆኔ እኮራበታለሁ፤” ብለዋል፡፡ በመቀጠልም “ይቅርታ መጠየቅ ካለብኝ የኦሮሞን ሕዝብ በደል በሚገባ ሳልገልጽ ቀርቼ ከሆነ፣ ወንድማማችነትንና አብሮ መኖርን አስቀድሜ ከሆነ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ለግል ጥቅምና ለዝና ያደረኩትም ካለ እግዚአብሔርን ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ሳላጠፋ የፈረደብኝን ፍርድ ቤት ቅጣቴን ያቃልልኛል ብዬ ይቅርታ መጠየቅ ባለመፈለጌ አዝናለሁ፤” ካሉ በኋላ፣ ባለቤታቸው ከሥራ እንዲወጡ በመደረጋቸው ልጆቻቸው ያለገቢ ለመኖር መገደዳቸውን አስረድተዋል፡፡ 

ሌሎቹም ተከሳሾች የቤተሰብ ኃላፊ መሆናቸውን፣ በሌላ ወንጀል ተጠይቀው እንደማያውቁ፣ ሕመምተኛ መሆናቸውንና ሌሎችንም ያቃልልናል ያሉዋቸውን ሐሳቦች ተናግረው የቅጣት ማቅለያ ሐሳባቸውን አጠቃለዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግም የቅጣት ማክበጃ ሐሳቡን ካቀረበ በኋላ፣ በጥፋተኞቹ ላይ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለኅዳር 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ችሎቱ አብቅቷል፡፡


Friday, November 2, 2012

November “Ethiopian Election Massacre” Commemoration Month


We remember and respect those fellow Ethiopians who gave their lives for their right to vote and for their vote to be counted.
On May 15, 2005, over 26 million Ethiopians voted peacefully to elect their leaders. As the results started to come in, showing a landslide victory for the opposition party, Meles Zenawi went on TV and declared a state of emergency. He also ordered re-votes in several districts where members of his party went down in defeat, banned political rallies, and unleashed his killers against peaceful citizens who protested his attempt to steal the election.
When the Addis Ababa Police showed restraint, Meles ordered all of them to be disarmed, and gave the Federal Police and his personal army, the Agazi, a shoot-to-kill order.
The Agazi and Federal Police snipers from roof tops and military trucks gunned down young, hundreds of unarmed protesters with 50 caliber rifles. Over 50,000 students and other individuals were rounded up and sent to concentration camps in remote parts of the country. All senior members of the opposition CUD were arrested. All the private press were shut down. The 2005 election massacre was one of the darkest moments in the history of Ethiopia.