Thursday, September 13, 2012

አና ጎሜዝ መለስ የሞቱት በሃምሌ መሆኑን አጋለጡ


(Sept. 12) የአውሮጳ ፓርላማ አባል የሆኑት አና ጎሜዝ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምንም እንኳን የሞቱት በሃምሌ (July) ወር መሆኑን አጋልጠው አንባገኑ የኢትዮጵያ መንግስት በሚስጥር ይዞ ጭቆናውን ለመቀጠል ሲሞክር እና ይፋዊ የስልጣን ሽግግር አለማድረጉን የአውሮፓ ፓርላማ በቸልታ መመልከቱ አግባብ አለሞሆኑን በቅርቡ በፓርላማው ስብሰባ ላይ ተናገሩ።
በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ጨቋኝ አገዛዝ እንዲቀጥል የማድረግ ሙከራ ለማስተካከል አለመጣሩ፤ ከአውሮፓ ሕብረት የጋራ የውጭና የደህንነት ስትራቴጂክ ጥቅም ጋር ይጋጫል ሲሉ ተናገሩ።
በአውሮፓ ህብረት ምክርቤት ስብሰባ ላይ ባነሱት ጥያቄ፤ በቅርቡ የተፈቱትን ሁለት ስዊድናዊ ጋዜጠኞች መፈታት አድንቀው፤ የአፍሪካ መቀመጫ፤ ከአፍሪካ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ፤ የአውሮፓ ህብረት ትልቋ እርዳታ ተቀባይ የሆነችው ኢትዮጵያ፤ ለአውሮፓ የጋራ የውጭና የጸጥታ ግንኙነት ትልቅ አጋር ብትሆንም፤ የአውሮፓ ህብረት፤ ሁለቱ የስዊድን ጋዜጠኞችም ይሁኑ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ምንም አይነት ጫናም ጥረትም አላደረገም ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከሞቱ ጀምሮ፤ ኢትዮጵያ ያለመንግስት ብትሆንም፤ እንዲሁም በስልጣን ላይ ያሉት ስብስቦች፤ አና ጎሜዝ “ጨቋኝ” ያሉትን አስተዳደር ለመቀጠል በሚስጢር እየዶለቱ ቢሆንም፤ የአውሮፓ ሕብረት ግን ጉዳዩን በዝታ እያለፈው ነው ብለዋል።
ስለዚህ፤ የአውሮፓ ህብረት፤ ስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት፤ በትጥቅ የሚታገሉትን ጨምሮ፤ ሁሉንም የፖለቲካ ሀይሎች ያሳተፈ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲጀምር ጫና እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
አና ጎሜዝ የአውሮፓ መንግስት ዝምታውን አቁሞ፤ የኢትዮጵያ አንድነት እንዲጠበቅ፤ የፖለቲካ ቀውስ ተፈጥሮ አገሪቱ ወደ ደም መፋሰስ እንዳታመራ እንዲያደርግ፤ ኢትዮጵያ ወደጨቋኝ አገዛዝ እንዳትመለስ ወይንም ጭቆናው እንዳይቀጥል፤ ይልቅስ ኢትዮጵያዊያን ሲመኙት የነበረው የዴሞክራሲያዊነት መንገድ እንዲቃና ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ፤ ለአፍሪካም፤ ለአለምም፤ ከአውሮፓ ህብረትም በጣም ጠቃሚ አገር ነች አሉት አና ጎሜዝ፤ የአውሮፓ ህብረት፤ በኢትዮጵያ ውስት እየተካሄደ ስላለው ፖለቲካዊ ክስተት ያላየ መምሰል የለበትም ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

No comments: