Wednesday, January 8, 2014

አርቲስት ነዋይ ደበበ በተወዛገበ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ የሙያ ጓደኞቹ ገለጹ




ከዓመታት በፊት በዋሽግተን ዲሲ ለሚታተመው ባውዛ ጋዜጣ “በ2001 ዓ.ም ወደ ሃገሬ እገባለሁ” በሚል ድምፃዊ ነዋይ ደበበ ሲናገር የቅርብ ወዳጅ አርቲስቶቹ “ሃገርህ መግባቱንስ ግባ፤ ግን ከሌሎቹ አርቲስቶች ተማር፤ አንተም ሃገርህ መግባትህን ግባ ግን ስለፖለቲካው ለየትኛውም የመንግስት ሚድያ አትናገር” የሚል ምክር ተሰጥቶት ነበር። ነዋይ ሲፈጥረው ግልጽ ሰው በመሆኑ የሚጠቅመውን እና የሚጎዳውን የሚያውቅ ሰው አይደለም እንደ ሙያ አጋሮቹ ገለጻ።
ይህ አርቲስት ለትዳሩ ፍቺ ያበቃውም ይኸው ግልጽነቱ ነው ይላሉ እነዚሁ ምንጮች። ለኮንሰርት ሌላ ሃገር ሄዶ ከአድናቂዎቹ ጋር ለሚስት የማይነገር ነገር ቢፈጽም እንኳ ለባለቤቱ ከመናገር አይደብቅም። “ሀመር መኪናዬን ይዤ ኢትዮጵያ ገባሁ” ብሎ ለሃገር ቤት ሚድያዎች ያወራውም ይኸው የሚነገር እና የማይነገር ነገርን ካለማወቁ የተነሳ ነው
ነዋይን በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ተዘዋውሮ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እንዲሰራ ካደረጉት ሰዎች ውስጥ አንዳንዶቹ ለዚህ ዜና ዘጋቢ እንደተናገሩት “ድምጻዊውን ለራሱ የማያውቅ” ሲሉ ይገልጹታል ከሌላ አርቲስቶች ጋር በማነጻጸር። ይኸው ድምፃዊ ኮንሰርት ተጠርቶ ከፕሮሞተሮች ከሰርን የሚል ምክንያት ሲቀርብለት ገንዘብ እንደማይጠይቅም ይነገርለታል። ሌሎቹ ስለመዝፈናቸው እንጂ ፕሮሞተሩ ከሰረ አለከሰረ ግድ እንደሌላቸው ያገናዝቧል። በዚህ ሁኔታ ነዋይ በኪሳራ ውስጥ ወደቀ፤ ሚስቱንም በትዳሩ ላይ ስለሚፈጽመው ነገር ስለማይደብቅ ሕይወቱ ተመሳቀለ። በዚህ ሁኔታ ወደ ሃገሬ በ2001 እገባለሁ ሲል ሲናገር በሙያ አጋሮቹ ተመከረ። “እባክህ ሃገርህ መግባትህን ግባ ግን በመንግስት ሚድያዎች ቀርበህ ባከበረህ ሕዝብ ፊት እንዳትዋርድ”
ነዋይ ሃገር ቤት ገና ከመግባቱ አዲስ አበባን ሳያያት ኤርፖርት ላይ ተቀበሉት።
እነ ራድዮ ፋና “ሃገሪቷን እንዴት አየሃት?” ሲሉ ጠየቁት
ሃገሪቱን ተዘዋውሮ ያላየውና ገና ከአውሮፕላን እንደወረደ የተናገረው ነዋይ የኢትዮጵያ ሕዝብ በልማት ውስጥ እንደሚገኝ፤ ሃገሪቱም እንደተለወጠች ተናገረ። ልብ በሉ ገና ከኤርፖርት ወርዶ አላየም።
ነዋይ ድሮ ሃገሩን እንዳልወደደና በሕዝብ እንዳልተፈቀረ ይህን ከተናገረ በኋላ በጣም ተናቀ። ከአሜሪካ በሚስቱ አማካኝነት ይዞት የነበረው ገንዘብ አለቀና አላሙዲንን ፍለጋ ሮጠ። በሸራተን ጋዝ ላይት የሚያመሹ የአላሙዲ ተላላኪዎች ነዋይ “አላሙዲንን አገናኙኝ” እያለ ሲለምመጥ እነሱ ይስቁበት ‘አላሙዲ አሁን በዚ አለፈ፤ በዚያ ሄደ” እያሉ ይስቁበት፤ ያቁለጨልጩት ጀመር። በሕዝብ የተከበረ ዘፋኝ በአላሙዲ ተላላኪዎች መሳለቂያ ሆነ።
ነዋይ ኢትዮጵያ ገብቶ በተቸገረበት ወቅት ራድዮኖች እየደወሉ ፕራንክ ኮል እያደረጉ ይሳለቁበት ገባ። በወያኔ መንግስት ፈቃድ ተሰጥቷቸው እየሰሩ የሚገኙ ራድዮኖች ነዋይን ፕራንክ እያደርጉ ሲሳለቁበት እንዴት ያሳቅቅ። ድሮ ይቃወምባቸው የነበሩ ወያኔዎች በሳቅቅቅ፣ ነዋይ ግን ስቅቅ። ነዋይ ግን አልገባውም። እንደውም ተወዛግቦ ራድዮኖቹ ለሱ ያዘኑ እየመሰለው ያለ የሌለውን ይቀባጥራል። “ሙዚቃ የሚያቀናብርልኝ አጣሁ” እያለም በግልጽ ፕራንክ ላደረጉት ራድዮኖች መጠላቱን ተናገረ። ይኸው ምስክርነቱ የነሰይፉ መሳቂያ ሲሆን፦
ነዋይ ምስኪን ነው። ሰው ሲስቅበት አያውቅም። ወያኔዎች እየተጠጉ “ጥሩ ሥራ ሰራህ you did good” ሲሉት ጥሩ እየመሰለው አቶ መለስን ሲቃወም እንዳልነበር ነጠላ ዜማም ሰራላቸው። የአቶ መለስ ሞት ሰሞን በወያኔ ደጋፊዎች ዘንድ የተሰጠው ሙገሳ ልቡን ነፍቶት እንደነበር የሙያ አጋሮቹ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ነዋይ ኢትዮጵያ ሄዶ ባለማወቅም ይሁን በማወቅ የሰራውን ስህተት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በመጣበት ጊዜ በደረሰበት ተቃውሞ ተደናግጦ “እኔ እኮ ለአቶ መለስ የዘፈንኩት ሰዎች አሳስተውኝ ነው” ሲል ተናገረ።
ነዋይ በነዋይ ይሳሳታል – ይህን አይተናል – ከአላሙዲ ፍራንክ ሲቀበል። ነዋይ በሴት ይታለላል – ለሚስቱ ተናገሮ ፈታዋለች። አላሙዲ ሊያስታርቁ ሲዊድን ድረስ ጠርተዋቸው የሆነውን ነገር ወደፊት እንጽፈዋለን። – ነዋይ በውዝግብ ላይ እንዳለ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ሲሄድ ከተመከረው ምክር፤ እዛ ከሄደ በኋላ ባለማወቅ በሰራው ስህተት፤ መለስ ከሞቱ በኋላ በተሸወደው ሽወዳ (እሱ እንዳለው) አይተናል።
ግን አሁንስ?
ያኔ ሁለት ጣቱን ለቅንጅት በመቀሰሩ የተነሳ የመንግስት ጋዜጠኞች ባገኙት ቁጥር ካሁን ካሁን ታሰርኩ ብሎ የሚበረግገው ነዋይ ደበበ፤ ለመለስ ብትዘፍን ያዋጣኻል – “እሺ”፤ ለአባይ ቦንድ ግዢ ኮንሰርት ዱባይ ሂድ “እሺ”… “እሺ” ባይ አርቲስት ሆኖ ቀረ። ሚስቱ የክሊኒክ ማናጀር አድርጋ አሜሪካ አስቀምጣው እንዳልነበር በርሷ ላይ ሲቀማጠል ተራ ሆኖ አረፈው። አሁን ከሰሞኑ ደግሞ በገና በዓል ዝግጅት ላይ አገራችን በዴሞክራሲ መመንጠቋንና የዘንድሮውን ገና በደርግ ዘመን ከነበረው ልዩ የሚያደርገው የአሁኑ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት መታጀቡ ስለመሆኑ ሲናገር እያየን ነው። አይ ነዋይ የአርቲስት ምሁርi እነ በቀለ ገርባ፣ እነ እስክንድር ነጋ፣ እነ አንዷለም አራጌ፣ ላሊሴ ኦልባና፣ ርዕዮት አለሙ የታሰሩት ዴሞክራሲ ስላለ ነው? ለነገሩ ነዋይ ካሳሳተው ነዋይ ምን ይጠበቃል?
እንደ ሙያ አጋሮቹ ገለጻ ከሆነ ነዋይን ወሰድ መለስ የሚያደርገው የአእምሮ መወዛገብ ከፍርሃት፣ ከፍቺና የሚጠብቅን ዝና ካለማግኘት ጋር የተይያዘው የአእምሮ ጭንቀት ነው።

No comments: