እየቆረቆረኝ ከሆዴ ሳይወጣ አደል ያለው ዘፋኙ፥
እኔ ባንድ አባባል አናለው፥ ሊነጋ ሲል ይጨልማል
ይገርማል ኢትዮጵያችን መቼም የቻለችው ጉድ አያልቅም ባለፈው ሰሞን የሃይማኖት አባቶች ናቸው የተባሉ ፋዘሮች ሰብሰብ አሉና የሂሳብ
ማሽናቸውን/ calculator/ ብድግ አርገው
በቃ በሂሳቡ ስሌት መሰረት ስንደምረው ወደኋላ መሄድ አልቻልንም እኛ ከዚህ በላይ አንለማመጥም አዲስ
የሃይማኖት አባት መምረጣችን ነው፥አቡነ መርቆሪዎስ አሻፈረኝ ብለዋል በፊትም በፍቃዳቸው ነው አልሰራም ብለው የሄዱት እያሉ በኢትዮጵያ
ህዝብ ፊት ያወሩት በቅርብ ነበር፥
በጣም የሚገርመው ግን የወያኔው ሌላ አባት አቶ
ግርማ ወልደጊዮርጊስ አንዴ አቡነ መርቆሪዮስ ወደስልጣነ መንበራቸው መመለስ ይችላሉ በፊትም እኮ ያ የማይረባ ታምራት ላይኔ ነው
ያባረራቸው ሲሉ ሰምተን ነበር፥፥
እኔ ምለው ግርም እያለኝ የመጣው ነገር የወያኔ
ነገር ነው፥ ውሸታቸው ከመብዛቱ የተነሳ ትላንትናና ዛሬ በተመሳሳይ ሰአት በዛው በፈረደበት ኢቲቪ ለዛው ለፈረደበት ህዝብ ሁለትና
ሶስት አይነት ውሸት በቡፌ መልክ ሲያቀርቡ እነዚህ ሰዎች ውሸታቸው ከመብዛቱ የተነሳ እያተምታታባቸው ነው ወይስ ማንም ምንም አያመጣም
ብለው ነው እያልኩ አንዳንዴ በሃሳብ ኢትዮጵያ ደርሼ እመጣለው፥፥
እኔ ግን የምለው እባካችው ወያኔዎች ቤተክርስቲያናችንን
ለቀቅ አርጉ ያለበለዚያ ያ ባለፈው ሰሞን ጀምሯችሁ የነበረው ፈንገል የሚያረገው በሽታ ማገርሸቱ አይቀሬ ነው፥፥
ዘማሪዋም እኮ ያለችው ይሄንኑ ነው፥_
አለው ነገር እግዚአብሄር እንዲህ አብዝቶ ዝም ካለ
ጠላቴ ሆይ ደስ አይበልህ ቢመሽም ለኔ ቀን አለ
አለው ነገር እግዚአብሄር እንዲህ አብዝቶ ዝም ካለ
ከሳሼ ሆይ ደስ አይበልህ ቢመሽም ለኔ ቀን አለ
ኢትዮጵያን እግዜር ይባርክ፥፥
ከጌዲዮን ኦስሎ
No comments:
Post a Comment